Recent Updates
  • እውነት? ሀሰት?

    ቀኑ መሸትሸት ብሏል። ፀሐይም ደከመኝ ብላ ወደ ጓዳዋ ገብታ የመንገድ ላይ መብራቶች በሥፍራዋ ተትክተዋል። አጎቴ ታናሽ ወንድሜን ስንት ሰዓት እንደሆነ ይጠይቀዋል። “አንድ ሰዓት ከአሥራ ሶስት ደቂቃ” ብሎ ይመልስለታል። አጎቴ መልሶ “ከሩብ አትልም እንዴ? ምንድነው ከአሥራ ሦስት ደቂቃ?” በማለት ያፋጥጠዋል። የእጅ ሰዓቱን መለስ ብሎ ሲያይ ከአሥራ ሦስት ወደ አሥራ ዐራት ባለመቀየሩ “ይኸው ከአሥራ ሶስት ደቂቃ እኮ አላለፈም ለምን ከሩብ እላለሁ? ይህ እኮ ውሸት ነው ይለዋል?” ወደ እኔ ዞሮ ዳኛ እመስል “አሁን ይሄ ልጅ ልክ ነው ትላለህ?” በማለት ይጠይቀኛል። ማነው ልክ? አጎቴ ነው እውነተኛ ወይስ ወንድሜ?
    አባታችን አብራም አብርሃም ከመሆኑ በፊትም ሆነ በኋላ እህት ሚስቱን ሳራን “እህቴ ናት” በማለቱ (ያውም እሷንም አሳምኖና ተባብረው) እና ሚስትነቷን ባለማሳወቁ አንድ ጊዜ ለፈርዖን ሌላ ጊዜ ደግሞ ለአቢሜሌክ አሳልፎ ሰጠ። ያው እግዜሩ በሱ ስለማይጨክን ነው መሰለኝ ፈርዖንን ቀጣው አቢሜሌክንም አስፈራራለት። አብርሃም ተረፈ ሚስቱም ተመለሰች።

    በሌላ ጊዜ ፈርዖን አዋላጆቹን ጠርቶ እንዲሁ “የያዕቆብ ዘር የሆነ ወንድ ከእናቱ ማሕጸን አይውረድልኝ፤ በዚያው አሰናብቱልኝ አለ”። እንግዲህ የመጀመሪያው በሕግ የተፈቀደ እና በቅዱሳት መጻሕፍት የተዘገበ ውርጃ መሆኑ ነው። አዋላጆቹም ከያዕቆብ ዘር ነበሩና አይ ወገናችን ሲያልቅ አናይም ይልቅ “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ሀገርህ ሴቶች እንዳይመስሉህ። ጠንካሮች ስለሆኑ እኛ ሳንደርስ እየወለዱ አስቸግረውናል።” እንለዋለን አሉ፤ አደረጉትም። ራሳቸውን ልጆቹንም አተረፉ። እግዚአብሔርም በዚህ ደስ ተሰኘ። መልካም አደረገላቸው ቤትም ሰራላቸው። ከፈርዖን ይልቅ እግዚአብሔርን መፍራታቸውን በ“ዋሾ”ነታቸው አሳዩ። ይህም በእግዚአብሔር አይን ግሩም ነበር።
    ደግሞ በሌላ ጊዜ እግዚአብሔር ሕዝቡን ብርቱ አድርጓል እና ኢያሪኮ ልትፈርስ ስትል ረዓብ ሀገሯን ከዳች። ዛሬ እንደሚደረገው ኹሉ ሰላዮቹን እያሉ “የሉም” ተኝተው “በዚህ በኩል ወጥተዋል” ብላ አስመልጣ ለራሷ(እና ለወገኗ) የቪዛ ትኬት አስመታች። ኢያሪኮ ስትተጠፋ እርሷ ተረፈች። በዚህ ሥራዋም ስትወደስ ኖረች። በቅዱሳት መጻሕፍትም በ”ዋሾ”ነቷ በቁጥር ጥቂት ተደርገው ከሚጠሩ ሴቶች መካከል ሆነች።

    እንዲሁ ኢያሱን አንድ ጊዜ የገባዖን ሰዎች እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ስለሆነ ጀግንነታችሁን ሰማን እንዳንጠፋ ከሩቅ ሀጋር ከእናንተ ጋር ቃልኪዳን ለመግባት ነው የመጣነው ብለው ያሻገቱትን እንጀራ ቀደው የሰፉትን የውሃመጠጫ ሌላውን አሳዩአቸው። ተራኪውም “ተንኮል” አደረጉ ብሎ አሞካሻቸው። እስራኤልም መሸወዱን ያወቀው ቆይቶ ነው። ጎረቤቶቻቸው ነበሩና።

    ስለ ሳሙኤል፣ ስለ ዳዊት፣ ስለ ሰብዓሰገሎቹ እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል። ጥያቄው ግን አሁንም ይቀጥላል። እውነት ምንድነው? ውሸትስ? እውነተኛስ ማነው? ውሸታሙስ?
    እውነት? ሀሰት? ቀኑ መሸትሸት ብሏል። ፀሐይም ደከመኝ ብላ ወደ ጓዳዋ ገብታ የመንገድ ላይ መብራቶች በሥፍራዋ ተትክተዋል። አጎቴ ታናሽ ወንድሜን ስንት ሰዓት እንደሆነ ይጠይቀዋል። “አንድ ሰዓት ከአሥራ ሶስት ደቂቃ” ብሎ ይመልስለታል። አጎቴ መልሶ “ከሩብ አትልም እንዴ? ምንድነው ከአሥራ ሦስት ደቂቃ?” በማለት ያፋጥጠዋል። የእጅ ሰዓቱን መለስ ብሎ ሲያይ ከአሥራ ሦስት ወደ አሥራ ዐራት ባለመቀየሩ “ይኸው ከአሥራ ሶስት ደቂቃ እኮ አላለፈም ለምን ከሩብ እላለሁ? ይህ እኮ ውሸት ነው ይለዋል?” ወደ እኔ ዞሮ ዳኛ እመስል “አሁን ይሄ ልጅ ልክ ነው ትላለህ?” በማለት ይጠይቀኛል። ማነው ልክ? አጎቴ ነው እውነተኛ ወይስ ወንድሜ? አባታችን አብራም አብርሃም ከመሆኑ በፊትም ሆነ በኋላ እህት ሚስቱን ሳራን “እህቴ ናት” በማለቱ (ያውም እሷንም አሳምኖና ተባብረው) እና ሚስትነቷን ባለማሳወቁ አንድ ጊዜ ለፈርዖን ሌላ ጊዜ ደግሞ ለአቢሜሌክ አሳልፎ ሰጠ። ያው እግዜሩ በሱ ስለማይጨክን ነው መሰለኝ ፈርዖንን ቀጣው አቢሜሌክንም አስፈራራለት። አብርሃም ተረፈ ሚስቱም ተመለሰች። በሌላ ጊዜ ፈርዖን አዋላጆቹን ጠርቶ እንዲሁ “የያዕቆብ ዘር የሆነ ወንድ ከእናቱ ማሕጸን አይውረድልኝ፤ በዚያው አሰናብቱልኝ አለ”። እንግዲህ የመጀመሪያው በሕግ የተፈቀደ እና በቅዱሳት መጻሕፍት የተዘገበ ውርጃ መሆኑ ነው። አዋላጆቹም ከያዕቆብ ዘር ነበሩና አይ ወገናችን ሲያልቅ አናይም ይልቅ “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ሀገርህ ሴቶች እንዳይመስሉህ። ጠንካሮች ስለሆኑ እኛ ሳንደርስ እየወለዱ አስቸግረውናል።” እንለዋለን አሉ፤ አደረጉትም። ራሳቸውን ልጆቹንም አተረፉ። እግዚአብሔርም በዚህ ደስ ተሰኘ። መልካም አደረገላቸው ቤትም ሰራላቸው። ከፈርዖን ይልቅ እግዚአብሔርን መፍራታቸውን በ“ዋሾ”ነታቸው አሳዩ። ይህም በእግዚአብሔር አይን ግሩም ነበር። ደግሞ በሌላ ጊዜ እግዚአብሔር ሕዝቡን ብርቱ አድርጓል እና ኢያሪኮ ልትፈርስ ስትል ረዓብ ሀገሯን ከዳች። ዛሬ እንደሚደረገው ኹሉ ሰላዮቹን እያሉ “የሉም” ተኝተው “በዚህ በኩል ወጥተዋል” ብላ አስመልጣ ለራሷ(እና ለወገኗ) የቪዛ ትኬት አስመታች። ኢያሪኮ ስትተጠፋ እርሷ ተረፈች። በዚህ ሥራዋም ስትወደስ ኖረች። በቅዱሳት መጻሕፍትም በ”ዋሾ”ነቷ በቁጥር ጥቂት ተደርገው ከሚጠሩ ሴቶች መካከል ሆነች። እንዲሁ ኢያሱን አንድ ጊዜ የገባዖን ሰዎች እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ስለሆነ ጀግንነታችሁን ሰማን እንዳንጠፋ ከሩቅ ሀጋር ከእናንተ ጋር ቃልኪዳን ለመግባት ነው የመጣነው ብለው ያሻገቱትን እንጀራ ቀደው የሰፉትን የውሃመጠጫ ሌላውን አሳዩአቸው። ተራኪውም “ተንኮል” አደረጉ ብሎ አሞካሻቸው። እስራኤልም መሸወዱን ያወቀው ቆይቶ ነው። ጎረቤቶቻቸው ነበሩና። ስለ ሳሙኤል፣ ስለ ዳዊት፣ ስለ ሰብዓሰገሎቹ እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል። ጥያቄው ግን አሁንም ይቀጥላል። እውነት ምንድነው? ውሸትስ? እውነተኛስ ማነው? ውሸታሙስ?
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares 8 Views
  • #housechurch #Jesusisthemessiah
    #housechurch #Jesusisthemessiah
    Love
    1
    0 Comments 0 Shares 12 Views
  • 0 Comments 0 Shares 10 Views
More Posts