April 23, 2026
አንበሳ ባንክ የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሶስተኛው ሩብ ዓመት እና የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አጠናቀቀ፡፡
(ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም) በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲደረግ የነበረው የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሶስተኛው ሩብ ዓመት እና የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡ ለሁለት ቀናት በቆየው ይህ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ የባንካችን ፕሬዝደንት አቶ ዳንኤል ተከስተ ባንኩ በሐብት አሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት፣ በውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ በዲጅታል ባንክ አገልግሎት (ተደራሽነት) እና በመሳሰሉት፤ በመገምገም […]
April 22, 2026
አንበሳ ባንክ የሶስተኛ ሩብ ዓመት እና የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ስብሰባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም) አንበሳ ባንክ እ.ኤ.አ. የ2025/26 በጀት ዓመት የሶስተኛ ሩብ አመት እና የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ስብሰባ በዋና መስሪያ ቤት መስብሰቢያ አዳራሽ በዛሬው ዕለት እያካሄደ ይገኛል፡፡ የባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ዳንኤል ተከስተ ስብሰባውን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የከፈቱ ሲሆን መልዕክቱን ተከትሎ የባንኩ የሶስተኛ ሩብ ዓመት እና የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በሪፖርቱ […]
February 3, 2026
የብራንድ ማኒፌስቶ ቪዲዮ
እንደ አንበሳ ባንክ አንበሳ በበላይነቱ፣ በግርማ ሞገሱ፣ በግሳቱ ብቻ ተወስኖ ይገለጻል የሚል ዕምነት የለንም በድፍረቱ፣ በጥንካሬው፣ በክብሩ ጭምር እንጂ፡፡ በሕይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት የጭረት ያክል ብልጭታ ለመፍጠር ድፍረቱ ያለው ሁሉ ለእኛ አንባሳ ነው፡፡ ይህ ዕምነት በአርማችን ውስጥ ይኖራል፡፡ እንደ አንበሳ ባንክ ከምቾት ይልቅ ትጋትን፣ ከፍርሃት ይልቅ መራመድን፣ ከማመንታት ይልቅ መጀመርን ከመረጡት ጎን እንቆማለን፡፡ ምክንያቱም ለውጥ […]
February 3, 2026
አንበሳ ባንክ አዲስ መለያ ይፋ አደረገ
አንበሳ ባንክ ከ18 አመታት ጉዞ በኋላ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ ሎጎ በአድዋ ሙዝየም በደማቅ ሁኔታ ይፋ አድርጓል።
January 23, 2026
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የስራ አመራር ስብሰባ ተጠናቀቀ
በሳፍየር አዲስ ሆቴል ላለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በዋና መስሪያ ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሪጅናል ፅ/ቤቶችና ዲስትሪክቶች መካከል ሲካሄድ የቆየው የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የስራ አመራር ስብሰባ በስኬት ተጠናቀቀ። በውይይቱ የስድስት ወራት አጠቃላይ ሪፖርት ቀርቦ ሰፋ ባለ መልኩ ግምገማ የተደረገ ሲሆን፤ የግማሽ ዓመቱ ውጤት ጠቅለል ባለመልኩ ሲታይ ብዙ ተሞክሮዎች የተቀሰሙበትና አመርቂ የተባለ የስራ […]
January 23, 2026
ሁለተኛ ቀን የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የግማሽ ዓመት የስራ አመራር ስብሰባ
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ሁለተኛ ቀን የስራ አመራር ስብሰባ ዛሬ የቀጠለ ሲሆን ስብሰባው በዛሬው እለት የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክየስኬትዎ አጋር!
January 23, 2026
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የግማሽ ዓመት የስራ አመራር ስብሰባ በማካሄድ ላይ ይገኛል
(ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም) አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ስብሰባ በማካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ስብሰባውን የባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ዳንኤል ተከስተ በንግግር ከፍተዋል፡፡አቶ ዳንኤል ተከስተ በንግግራቸው ስብሰባው ውጤታማ እንዲሆን እና የባንኩን የወደፊት አቅጣጫ ለመቀየስ እንዲቻል ተሳታፊዎች ያልተቆጠበ ገንቢ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያበረታቱ ሲሆን የባንኩ የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም በባንኩ ፕላኒንግ እና ስትራቴጂ መምሪያ […]
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ንስር ማይክሮ ፋይናንስ በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ንስር ማይክሮ ፋይናንስ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ሪቴል ባንኪንግ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሚካኤል ገዛኢ እና በንስር ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ እምባለ በተፈረመው ስምምነት መሰረት ባንኩ የፋይናንስ አካታችነትን ለማስፋት የፋይናንስ ተቋማት ባልተዳረሳባቸው እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ […]
December 6, 2025
22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ተከበረ
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር -ተቋምን በአሰራር!” በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሕዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አክብረዋል።በክብረ በዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ የሪቴል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሚካኤል ገዛኢ እንደገለፁት ሙስና ዘርፈ ብዙ እና በተለያዩ ጊዜያቶች ይዘቱን ቀይሮ የሚመጣ መሆኑን በመገንዘብ […]
November 14, 2025
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የዓዲግራት ከተማ አስተዳደር በከተማ ውበት እና ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
(ሕዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም) አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከዓዲግራት ከተማ አስተዳደር ጋር በከተማ ውበት እና ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው ዕለት የተፈራረሙ ሲሆን በስምምነቱ መሰረትም ባንኩ የሚያለማውን ቦታ ከከተማ አስተዳደሩ ተረክቧል፡፡ የስምምነት ፊርማውን እና የሳይት ርክክቡን የባንኩ ግእዝ ሪጅን ተ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉአለም ከበደ እና የዓዲግራት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔር የፈጸሙ ሲሆን […]
